በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) በአደረባቸው ህመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
የፕሮፌሰር በየነን ሕልፈተ-ሕወት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡
በአስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልዕክትም÷ በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) በኢትዮዽያ ገንቢ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምልክት ነበሩ ብለዋል።
ረዘም ላለ ጊዜ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስሰማ ከልብ አዝኛለሁ ሲሉም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
ያቆዩት ውርስ እና ቅርስ ፀንቶ እንዲቀጥል ነፍሳቸውም በሰላም እንድታርፍ እመኛለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)።