የኢትዮጵያ የቱሪዝም ሳተላይት አካውንት ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ማስረጃን መሰረት ያደረገ ፖሊሲ መቅረፅና ውሳኔ መስጠት የሚያስችል የቱሪዝም ሳተላይት አካውንት ይፋ ሆነ፡፡
የዓለም የቱሪዝም ቀንን በማስመልከት ከኢጋድ እና ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ኤግዚቢሽን በዓድዋ ድል መታሰቢያ መካሄድ ጀምሯል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የቱሪዝም ሳተላይት አካውንቱን ይፋ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሳተላይት አካውንት ማስረጃን መሰረት ያደረገ ፖሊሲ ለመቅረፅና ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።
ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቱሪዝም እና የስታስቲክስ ክፍሎች፣ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት እና አጋር ተቋማት ጋር በትብብር የተዘጋጀው የቱሪዝም ሳተላይት አካውንት ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በላይ ጊዜ ወስዷል ተብሏል።
የሳተላይት አካውንቱ መረጃዎችን በመሰነድና በማስቀመጥ ከቱሪዝም ዘርፍ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ አቅም በአግባቡ መጠቀም እንደሚያስችል ተገልጿል።