በሀገራዊ ምክክር ሂደት ከወጣቶች ምን ይጠበቃል?
አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገራዊ ምክክር ሂደት ከወጣቶች በርካታ ጉዳዮች እንደሚጠበቁ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስገንዝቧል፡፡
ቀጥለው የተዘረዘሩትን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮች ከወጣቶች እንደሚጠበቁ የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡
- የተለያዩ መዋቅሮችን በመጠቀም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና በመኖሪያ አካባቢዎች ውስጥ በመሰባሰብ ሐሳቦቻቸውን ማንሸራሸር እና ማዳበር፤
- ውይይት እና ንግግርን በሚያበረታታ እና መከባበርን መርህ ባደረገ መልኩ የሐሳብ ልዩነቶችን እና አለመግባባቶችን በምክክር የመፍታትን ባህል ማዳበር፤
- በርህራሄ፣ በመደማመጥ የማይግባቡባቸውን ጉዳዮች በመለየት ለሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ግብዓት መስጠት፤
- በሥነ-ምክክር ዙሪያ በቂ ግንዛቤን በመውሰድ ሌሎች ዜጎች የሀገራዊ ምክክር ዘለቄታዊ ጠቀሜታን እንዲረዱ ማድረግ፤
- ሀገራዊ መግባባት ሊደረግባቸው ይገባል የሚባሉ ጉዳዮችን በመለየት በተለያዩ የበይነ-መረብ አማራጮች ኃላፊነት በተሞላው መልኩ ሐሳቦችን ማንሸራሸር እና መወያየት፤
- በተለያዩ ውይይቶች ያዳበሯቸውን የአጀንዳ ሐሳቦች በቡድን ወይም በግል ሆነው ለኮሚሽኑ ማቅረብ (በአካል፣በኢሜል፣ በፖስታ፤ እና በድረ-ገፅ)
አጀንዳ ለመስጠትም፡-
- ድረ ገጽ፡- በፖስታ ሳጥን ቁጥር፡ 32623 አዲስ አበባ ወይም
- በኢሜል፡ contact@ethiondc.org ወይም
- በኮሚሽኑ ድረ-ገፅ፡ https://ethiondc.org.et መጠቀም ይችላሉ፡፡
ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!