Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣና ሀይቅ የእምቦጭ አረምን ለመከላከል የሚውል የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጣና ሀይቅ ለይ ለተከሰተው የእምቦጭ አረም ለመከላከል የሚውል የ10 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

“ጣናን እንታደግ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ የወጣቶች የበጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ አስተባባሪነት ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ እና ቁጥራቸው ከ100 በላይ የሆኑ ወሰን የለሽ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶች ዛሬ በባህር ዳር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጥተዋል።

ከዚሁ ጎን ለጎንም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእንቦጭ ዓረም መከላከል የሚረዳ የ10 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍም ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ድጋፍ አበርክቷል።

በገንዘብ ርክክቡ ላይ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትርና ወይዘሮ ፍልሰን አብዱላሂ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳድር ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት አስተባባሪ ኢንጅነር እንዳወቅ አብቴን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በርክክቡ ወቅት ንግግር ያደረጉት  ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስተር ፌልሰን አብዱላሂ፥ የአዲስአበባ የበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም ለመከላከልና ጣናን ለመታደግ የእያደሩት ያለውን ስራ የሚያስመሰግናቸው ነው ብለዋል።

ወደፊትም በእነደዚህ አይነት በጎ ተግባራት ላይ ከጎናቸው እንደሚሆኑ  ገለፀዋል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት አስተባባሪ ኢንጅነር እንዳወቅ አብቴ በበኩላቸው፥ ጣናን ከተጋረጠበት የእንቦጭ መጤ አረም እና መሰል አደጋዎች መከላከል የሁላችንም ኃላፊነትና ግዴታ ብለዋል።

ይህንኑ ርብርብ ሊረዳ በሚችል መልኩ ሁላችንም ችግኞችን በመትከል በአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ላይ መሳተፍ ያስፈልጋል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

በናትናኤል ጥጋቡ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.