ፋና ስብስብ

በአርሲ ዞን በተከራዩ ላይ የ500 ብር የኪራይ ዋጋ የጨመረው አከራይ በ10 ሺህ ብር ተቀጣ

By Tibebu Kebede

June 27, 2020

አከራዩ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመተላለፍ በተከራይ ላይ የቤት ክራይ ዋጋ በመጨሩ መቀጣቱን ከአርሲ ዞን ፖሊስ ኮሙኒኬሽን ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ የህዝብ ግንኙነት በፌስቡክ ገፁ ባሰፈረው ጽሁፍ አመልክቷል።

ግለሰቡ ግንቦት 11 2012 ዓ.ም ከጥዋቱ 4 ሰዓት ሲሆን አርሲ ዞን፣ሙኔሳ ወረዳ ቀርሳ ከተማ ውስጥ የቤቱ ተከራይ ግለሰብ በፊት ከሚከፍለው 500 ብር ላይ 500 ብር በመጨመር 1 ሺህ ብር እንዲከፍል አሊያም ከቤቱ እንዲወጣ መጠየቁን ነው መረጃው የሚያመለክተው።

አከራዩ በዚህም የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ተላልፎ በመገኘቱ የወረዳው ፖሊስ ጉዳዩን በማስረጃ በማስደገፍ የምርመራ መዝገቡን ለፍርድ ቤት ማቅረቡ ተገልጿል፡፡

የአርሲ ዞን ሙኔሳ ወረዳ ፍርድ ቤትም የቤት አከራዩ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ10 ሺህ ብር እንዲቀጣ የወሰነበት መሆኑን ከአርሲ ዞን ፖሊስ ኮሙኒኬሽን ጉዳይ ምክትል ኮማንደር ጎሳ አማን አስታውቅዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።