Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (ኦ ቢ ኤን) ሆርን ኦፍ አፍሪካ ቻናል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (ኦ ቢ ኤን) ሆርን ኦፍ አፍሪካ ቻናል እና የኦቢቫን ዘመናዊ ኤችዲ (HD) ተንቀሳቃሽ ማሰራጫን መርቀዋል፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የፌደራል እና የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ተገኝተዋል፡፡

ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ በ 8 ቋንቋዎች ስርጭት እያካሄደ የሚገኝ ጣቢያ ሲሆን ÷በቀጣይ በተጨማሪ ቋንቋዎች አገልግሎት ለመስጠት እቅድ እንዳለው ከጣቢያው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተያያዘ የወሊሶ፣ አምቦ፣ እና ባሌ ሮቤ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.