ዓለምአቀፋዊ ዜና

ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከግማሽ ሚሊየን አልፏል

By Tibebu Kebede

June 29, 2020

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከግማሽ ሚሊየን ማለፉ ተነገረ።

ከዚህ ውስጥ በአሜሪካ 125 ሺህ 803 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመላክታል።

በብራዚል ደግሞ 57 ሺህ 622 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት ተዳርገዋል።

ብሪታንያ፣ ጣሊያን ስፔን ደግሞ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።

በተያያዘም ዓለም ላይ ኮሮና ቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 10 ሚሊየን አልፏል።

አሁን ላይ በአሜሪካ በ30 ግዛቶች ቫይረሱ እንደ አዲስ እያገረሸ መሆኑም ተገልጿል።

በቻይና ሄቤይ ግዛት ደግሞ 400 ሺህ ሰዎች በአስገዳጅ የእንቅስቃሴ ገደብ ውስጥ ይገኛሉም ተብሏል።

ምንጭ፡- ቢቢሲ