Fana: At a Speed of Life!

ጃፓን በኢትዮጵያ ኮቪድ19ን ለመከላከል የሚውል 4 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጃፓን የመንግስታቱ ድርጅት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በኢትዮጵያ የኮቪድ19 ወረርሽኝ ተፅዕኖን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ የሚውል 4 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለገሰች።

ድጋፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዙ የኢንፌክሽን መከላከያ፣ የመጠጥ ውሃና የስነ ንጽህና እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችን አቅም ማሳደግ የሚያስችል ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም በኮቪድ19 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን መስራትም የድጋፉ አካል መሆኑን ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ አስታውቋል።

የአሁኑ ድጋፍ ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ 750 ሺህ ለሚሆኑ ህፃናትና ሴቶች የንጹህ መጠጥ ውሃ እንዲሁም የጤና እና ንፅህና አጠባበቅ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የሚከናወነውን ጥረት ያግዘዋል ተብሎ ታምኖበታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.