የሀገር ውስጥ ዜና

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 18ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል

By Feven Bishaw

June 29, 2020

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 18ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል፡፡

ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ነገ በሚያካሂደው ስብሰባው የምክር ቤቱን 5ኛ አመት የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ በማጽደቅ ይጀምራል ተብሎ የጠበቃል፡፡