የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ለአዲሱ የማላዊ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

By Feven Bishaw

June 29, 2020

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአዲሱ የማላዊ ፕሬዚዳንት ዶክተር ላዛረስ ቻክዌራን የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ከአዲሱ ፕሬዚዳንት ጋር በሁለትዮሽ እንዲሁም በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ አብረው እንደሚሰሩ እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል።