የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 867 ደረሰ

By Feven Bishaw

June 29, 2020

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ 132 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በዛሬው እለት በሃገር አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 157 ሰዎች ውስጥ 132 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ በአጠቃላይም በመዲናዋ 3 ሺህ 867 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።