የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ያገኙት የኖቤል የሰላም ሽልማት ሜዳሊያና ዲፕሎማ ቅጂ በሰላም ሚኒስቴር ተቀመጠ

By Tibebu Kebede

December 17, 2019

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ካገኙት የኖቤል የሰላም ሽልማት ሜዳሊያና ዲፕሎማ ቅጂ ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆን በሰላም ሚኒስቴር ተቀመጠ።

የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት መሪዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የማስቀመጥ ስነ ስርዓቱ ተከናውኗል።