ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቱርክ ከጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ግድያ ጋር በተያያዘ 20 ተጠርጣሪዎችን ፍርድ ቤት አቀረበች

By Tibebu Kebede

July 03, 2020

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቱርክ ከጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ግድያ ጋር በተያያዘ 20 ተጠርጣሪዎችን ፍርድ ቤት አቀረበች።

ተጠርጣሪዎቹ 20 የሳዑዲ ዓረቢያ ዜጎች ሲሆኑ ዛሬ በቱርክ ፍርድ ቤት ቀርበው ምርመራ ተጀምሮባቸዋል።

የጋዜጠኛ ጀማሌ ካሾጊ እጮኛም ፍርድ ቤት ቀርባ ምስክርነቷን ሰጥታለች።

በወቅቱም የጋዜጠኛው እንቅስቃሴ በተለያዩ ማስጠንቀቂያዎችና ማስፈራሪያዎች የታጀበ እንደነበር አስረድታለች።

ከጋዜጠኛው ግድያ ጀርባ የሳዑዲ ዓረቢያ እጅ እንዳለበት ቀደም ብሎ ሲነገር ቆይቷል።

ዛሬ ቱርክ የጀመረችው ምርመራ የወንጀሉን ምንጭ ያመላክታል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፡- አልጀዚራ