Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አባባ ከተማ የንግድ ተቋማትም ሆኑ የግልና የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወደ እንቅስቃሴ ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አባባ ከተማ ዛሬ ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ የንግድ ተቋማትም ሆኑ የግልና የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴ ገብተዋል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች ባደረገው ቅኝት ተቋማትም ሆኑ የትራንስፖርት እንቅስቃሴው እንደወትሮው በሰላማዊ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን መታዘብ ችሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በከተማዋ ከሰሞኑ ተቀዛቅዞ የነበረው እንቅስቃሴ ከዛሬ ጀምሮ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እንዲመለስ መግለጻቸው ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም ዛሬ ተቋማት ስራዎቻቸውን ሲያከናውኑ የዋሉ ሲሆን፤ በተመሳሳይም የንግድ ተቋማት ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዎች ተመልሰዋል።

በከተማዋ ሸገር ትራንስፖርትና አንበሳ የከተማ አውቶብስን ጨምሮ የሚኒባስ ታክሲዎችም መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።

አስተያየታቸውን ለጣቢያችን የሰጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችም በመዲናዋ ዛሬ የተመለሰው መደበኛ ሰላማዊ እቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.