Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት 178 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3 ሺህ 315 የላብራቶሪ ምርመራ 178 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በቫይረሱ በምርመራ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥም 133 ሰዎች ከአዲስ አበባ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አመላክቷል።

እንዲሁም 15 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 9 ሰዎች ከጋምቤላ ክልል፣ 6 ሰዎች ከሀረሪ ክልል፣ 5 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 2 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 2 ሰዎች ከሲዳማ ክልል፣ 1 ሰው ከድሬዳዋ አስተዳደር እንዲሁም 1 ሰው ከአፋር ክልል ናቸው።

ከዚህ ባለፈ በትናንትናው እለት የ2 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ መሆኑንም ሚኒስቴሩ ባወጣው እለታዊ ሪፖርት አመላክቷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 116 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ መሆኑንም ነው ሚኒስቴሩ የጠቆመው።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.