Fana: At a Speed of Life!

የከሸፈ የሴራ ፖለቲካን የሚያራምዱ ኃይሎች ወደ ራሳቸው ሊመለሱ ይገባል- የኦሮሚያ ክልል መንግስት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የከሸፈ የሴራ ፖለቲካን የሚያራምዱ ኃይሎች ወደ ራሳቸው ሊመለሱ እንደሚገባ የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አሳሰበ።

ቢሮው ትናንት ማምሻውን በሰጠው መግለጫ፥ አርቲስትና የመብት ተሟጋች የሆነውን ሃጫሉ ሁንዴሳን በማስገደል ለማስቀጠል የተሞከረውን የሴራ ፖለቲካ መምከኑንም ገልጿል።

መግለጫውን የሰጡት የቢሮው ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ፥ ሴራውን ተከትሎ በተከሰተው ሁከት ለጠፋው የሰው ህይወትና ንብረት ውድመት የክልሉ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማው አስታውቅዋል።

ጉዳት የደረሰባቸዉን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም  ክልሉ በየደረጃዉ ኮሚቴዎችን አቋቁሞ እየሰራ እንደሆነም፣ የክልሉ መንግስትን ሃሳብ ያንጸባረቀው መግለጫ አንስቷል።

አጥፊዎችን ለህግ ለማቅረብና በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ከፌደራል መንግስት ጋር እየተሰራ እንደሆነም አቶ ጌታቸው አብራርተዋል።

ከሰሞኑ በክልሉ የተለያዮ አካባቢዎች ተቃዉሞ ለማስነሳት በሴረኞች የታለመዉ እቅድ  በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት በማጣቱ መክሸፉንም ተናግረዋል።

በአወል አበራ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.