የአትሌት አበበ ቢቂላ መታሰቢያና 14ኛው የካሳማ የግማሽ ማራቶን ውድድር ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአትሌት አበበ ቢቂላ መታሰቢያና 14ኛው የካሳማ ከተማ የግማሽ ማራቶን ውድድር ተካሄደ።
በውድድሩ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች አሸንፈዋል።
በግማሽ ማራቶን ውድድሩ በወንዶች አትሌት አብዮት አብነት እንዲሁም በሴቶች ደግሞ አትሌት እታለማሁ ስንታየሁ አሸናፊዎች ሆነዋል።
ውድድሩን አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ አቶ ቢልልኝ መቆያና የአትሌት አበበ ቢቂላ ልጅ የትናየት አበበ አስጀምረውታል።
መረጃው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው