የሀገር ውስጥ ዜና

በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የተጠረጠሩ 2 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

By Tibebu Kebede

July 10, 2020

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አዳነች አቤቤ በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የተጠረጠሩ 2 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናገሩ።

ጠቅላይ ዐቃቤ ህጓ በሰጡት መግለጫ 1ኛ ተጠርጣሪ ጥላሁን ያሚ እና 2ኛ ተጠርጣሪ አብዲ አለማየሁ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

3ኛ ተጠርጣሪ የሆነው ከበደ ገመቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እየተደረገ መሆኑንም በመግለጫቸው አንስተዋል።

ህብረተሰቡም ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል በሚደረገው ጥረት ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

1ኛ ተጠርጣሪ ጥላሁን ያሚ ለፖሊስ በሰጠው የእምነት ክህደት ቃል ተኳሽ መሆኑን እና ከኦነግ ሸኔ ተልዕኮ መቀበሉን አምኗል።

ግለሰቡ ተልዕኮውን ከሁለት ሰዎች መቀበሉንም ነው ያመነው።

በመግለጫቸው መንግስት ህግ የማስከበር ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አውስተዋል።

በብስራት መለሰ