Fana: At a Speed of Life!

ከ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኞች በስተቀር ሁሉም ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ የትምህርት ደረጃ ያለፈተና እንዲዘዋወሩ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ክልላዊ እና ሀገር አቀፍ ፈተና ወሳጆች በስተቀር ሁሉም የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ የትምህርት ደረጃ ያለምንም ፈተና እንዲዘዋወሩ ተወሰነ።

ያለፈተና የተዘዋወሩ ተማሪዎች የማካካሻ ትምህርት እንደሚሰጣቸውም የትምህርት ሚኒስቴር በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ እንዳስታወቁት ክልላዊ እና ብሄራዊ ፈተና የሚወስዱት ተማሪዎች ደግሞ ትምህርት በሚጀመርበት ወቅት የ45 ቀን የማካካሻ ትምህርት ከወሰዱ በኋላ ፈተናውን የሚወስዱ ይሆናል።

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተናውን በቀጥታ (ኦንላይን) ለመስጠት የትምህርት ቤቶች ልየታ እና ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ቤቶች ምዝገባ የሚጀምሩት ከነሃሴ ወር መጨረሻ ሳምንት ጀምሮ እንደሚሆንም ገልጸዋል።

የግል ትምህርት ቤቶችም በቀጣይ አመት የትምህርት ክፍያ ላይ መጨመር እንደማይችሉም በመግለጫቸው አሳስበዋል።

በአወል አበራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.