የሀገር ውስጥ ዜና

በአርቲስት ሃጫሉ ግድያ ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረው ከበደ ገመቹ በቁጥጥር ስር ዋለ

By Tibebu Kebede

July 11, 2020

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረው  ከበደ ገመቹ በቁጥጥር ስር መዋሉን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ።

ጠቅላይ አቃቤ ህግ ትናንት ማምሻውን ባወጠው መግለጫ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር የዋለው በአደኣ አካባቢ ልዩ ስሙ ድሬ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ነው።

የኦሮሚያ ፖሊስ ፌዴራል ፖሊስና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከአካባው ነዋሪ ጋር በመሆን  በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተጠቁሟል።

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የተጠረጠሩ 2 ሰዎች ትናንትና በቁጥጥር ስር መዋላቸውን መናገራቸው ይታወሳል።

1ኛ ተጠርጣሪ ጥላሁን ያሚ እና 2ኛ ተጠርጣሪ አብዲ አለማየሁ መሆናቸውም ነው ተገለፀው።