Fana: At a Speed of Life!

አርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ከመገደሉ በፊት የኦነግ ሸኔ አባላት በአርቲስቱ ቴሌግራም አድራሻ በጽሁፍና በድምፅ የላኩለትን የግድያ ዛቻ በማስረጃነት መያዙ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ከመገደሉ በፊት የኦነግ ሸኔ አባላት በአርቲስቱ ቴሌግራም አድራሻ በጽሁፍና በድምፅ የላኩለትን የግድያ ዛቻ በማስረጃነት  መያዙን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ይፋ አደረገ።

አቃቤ ህግ በትናትናው ዕለት በስጠው መግለጫ ÷ ከአርቲስቱ ግድያ በኋላ አስክሬኑን ለመቀማት በተደረገው ጥረት አቶ በቀለ ገርባ ቡራዩ ለሚገኙ ሁለት ወጣቶች በመደወል አስክሬኑን ወደ አዲስ አበባ እንዲያመጡት ማዘዛቸውንም የሚያሳይ ማስረጃ መያዙን አስታውቋል።

እንዲሁም በተለይ አርቲስቱ ከኦ ኤም ኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ቃል ምልልስ ካደረገ በኋላ በተደጋጋሚ ከኦነግ ሸኔ ዛቻዎችና ማስፈራሪያ ይደርሰው እንደነበርም ታውቋል።

ከደዴሳ አካባቢ በመደወልም የኦነግ ሽኔ አባል መሆኑን በመግለፅ መሰል ማስፈራሪያ ይስነዘርበት እንደነበር ተግልጿል።

ተጠርጣሪው ከለውጡ ወዲህ የኦሮሞ ህዝብ እየተጠቀመ አይደለም የምትገድለው ሰው አለ ይሄን ካደረክ ለአንተና ለኦሮሞ ያልፍለታል መባሉን በእምነት ቃሉ ለፖሊስ መስጡን ተገልጿል።

ሆኖም የሚገድለው ሰው አርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ መሆኑን እንደማያውቅ ተናግሯል ተጠርጣሪው።

በተቃራኒው ከኦ ኤም ኤን ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ 1 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ቢሆንም 45 ደቂቃው መቆረጡ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም  በተቆጠረው ቃል ምልልስ ውስጥ የኦነግ ሸኔ አባላት ይዝቱበት እንደነበር አርቲስቱ ተናግሯል።

 

በጥበበስላሴ ጀንበሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.