Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከደቡብ ክልል የፌደራል፣ የክልል እና የዞን አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከደቡብ ክልል የፌደራል፣ የክልል እና የዞን አመራሮች ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአመራሮቹ ጋር በክልሉ ሰላም፣ ልማት፣ የአደረጃጀት ጥያቄዎችና በሃገር ግንባታ ዙሪያ ላይ ነው ውይይት ያደረጉት።

በውይይቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀደም ሲል የነበረው የክልሉ አደረጃጀት ችግር የነበረበትና እስከ ለውጡ ዋዜማ ድረስ ጥያቄ ይነሳበት እንደነበር አንስተዋል።

የክልሉ አመራር ለሃገራዊ ለውጡ በግንባር ቀደምነት የታገለ ቢሆንም አሁን ላይ በክልሉ ለሚታየው የፀጥታ መደፍረስ ችግር በዋናነት የአመራሩ ድክመት መሆኑንም ገልፀዋል።

በውይይቱ ላይ በደቡብ ክልል ለተነሱ ጥያቄዎች የመፍትሄ ሀሳቦችና አቅጣጫዎች መቀመጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.