ዓለምአቀፋዊ ዜና

በተያዘው የፈረንጆች ዓመት የተፈጸመው ዓለም አቀፍ የብድር መጠን ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል

By Tibebu Kebede

July 13, 2020

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በተያዘው የፈረንጆች ዓመት የተፈጸመው ዓለም አቀፍ የብድር መጠን ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ።

እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) መረጃ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እና በቫይረሱ ሳቢያ የደረሰባቸውን የኢኮኖሚ ቀውስ ለማነቃቃት ከፍተኛ መጠን ያለው ብድር ሲወስዱ ቆይተዋል።

ይህን ተከትሎም በ2020 ሀገራት የፈጸሙት የብድር መጠን በታሪክ ከፍተኛ ሆኖ መመዝገቡን ነው ድርጅቱ ያስታወቀው።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከኢኮኖሚው ባሻገር በሰው ልጆች ላይ ሁለን አቀፍ የሆነ ማህበራዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ማድረሱን መረጃዎች ያመላክታሉ።

አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ 12 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ዜጎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው÷ ከ555 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል።

በሌላ በኩል 6 ነጥብ 7 ሚሊየን የሚሆኑ ዜጎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፣ ቢቢሲ