Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ተቋርጦ የነበረውን የኮርፖሬሽኑን የቤት ግንባታ መርሃ ግብር አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ባለፉት 28 ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የኮርፖሬሽኑን የቤት ግንባታ መርሃ ግብር አስጀመረ።

ኮርፖሬሽኑ በአሁኑ ወቅት በሁለት ዙር የተለያዩ የቤት ግንባታዎችን እያከናወነ ይገኛል።

በመጀመሪያው ዙር በአምስት የተለያዩ የግንባታ ስፍራዎች ለመኖሪያና ለንግድ የሚሆኑ ቤቶች ግንባታ ያከናውናል።

በሁለተኛው ዙር ደግሞ በአራት የግንባታ ስፍራዎች የተለያዩ የቤት ግንባታዎችን እንደሚያከናውን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል ተናግረዋል።

ኮርፖሬሽኑ አሁን እያስገነባቸው ካሉ ቤቶች በተጨማሪ በስሩ ያሉና እድሳት የሚፈልጉ ከ20 በላይ ህንጻዎችን አሳድሷል።

በአሁኑ ወቅት የኮርፖሬሽኑ የሀብት መጠን 71 ቢሊየን ብር ይገመታል።

በጥበበስላሴ ጀንበሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.