ዓለምአቀፋዊ ዜና

በፖላንድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አንድሬዥ ዱዳ አሸነፉ

By Tibebu Kebede

July 13, 2020

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፖላንድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አንድርዥ ዱዳ አሸናፊ ሆነዋል።

ፕሬዚዳንት ዱዳ ትናንት በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተቀናቃኛቸው የሆኑት ራፋል ትርዛስኮውስኪን በጠባብ ልዩነት ማሸነፋቸው ተነግሯል።

የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽንም ፕሬዚዳንት ዱዳ ምርጫውን 51 ነጥብ 2 በመቶ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸውን አስታውቋል።

አሁን ላይ ከአጠቃላይ ድምጽ አሰጣጡ 99 በመቶው መቆጠሩም ተገልጿል።

በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የምስራቅ አውሮፓዋ ሃገር ከአውሮፓ ህብረት ጋር የሚኖራት ግንኙነት ዋነኛ አጀንዳ ነበር ተብሏል።

ፕሬዚዳንቱ ከፅንስ ማስወረድና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ጋር በተያያዘ በያዙት አቋም ሳቢያ ከበርካቶች ተቃውሞና ትችት ማስተናገዳቸው ይነገራል።

የአሁኑ የምርጫ ውጤት የኮሙዩኒዝም ስርአት ከተወገደበት የፈረንጆቹ 1989 በኋላ እጅግ ጣባቡ ነው ተብሏል።

ምንጭ፡- ቢቢሲ