ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በብሪክስ ጉባኤ ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የመነጋገር መልካም እድል አግኝተናል ብለዋል።