የሀገር ውስጥ ዜና

ለአዲስ አበባ መንገዶች ጥገና የሚውል የ386 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ

By Tibebu Kebede

December 17, 2019

አዲስ አበባ ታህሳስ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ጃፓን ለአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ጥገና የሚውል የ386 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ማትሱናጋ ዳይሱኬ ተፈራርመውታል።