በደንበኞቼ ሠነዶች ላይ ጉዳት አልደረሰም- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ሸማ ተራ በነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማኅበር ሕንጻ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ የደንበኞቹ ሠነዶችና መረጃዎች ጉዳት እንዳልደረሰባቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አረጋገጠ፡፡
አደጋውን ተከትሎ ሸማ ተራ ቅርንጫፍ ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት እንደማይሰጥም የባንኩ መረጃ አመላክቷል፡፡
በመሆኑም በቅርንጫፉ ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት በአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ እና በአቅራቢያው በሚገኙ ሌሎች ቅርንጫፎች እየሰጠ መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡