Fana: At a Speed of Life!

ለአሰልጣኝ አስራት ሃይሌ የሽኝት መርሐ ግብር ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሰልጣኝ አስራት ሃይሌ የአስክሬን ሽኝት መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም ተከናውኗል፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በተጫዋችነትና አሰልጣኝነት ለረጅም ዓመታት ያገለገለው አስራት ሃይሌ (ጎራዴው) ከትናንት በስቲያ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወቃል፡፡

በዛሬው እለትም ወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት በአዲስ አበባ ስታዲየም የሽኝት መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ውጣ ውረድን አልፎ በርካታ ድልን በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት የተቀዳጀ ጠንካራ የስፖርት ሰው የነበረ ሲሆን÷ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ጨምሮ የተለያዩ ክለቦችን በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት በማገልገል በርካታ ዋንጫ አንስቷል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.