Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ የሥራ ሃላፊዎች የከተማዋ ፖሊስ ያከናወናቸውን የሪፎርም ስራዎች ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መካከለኛና ከፍተኛ አመራሮች የአዲስ አበባ ፖሊስ ያከናወናቸውን የሪፎርም ስራዎች ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ በቅት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው÷የአዲስ አበባ ፖሊስ መዲናዋን የሚመጥን ተቋምን መገንባት ስራ ላይ ያተኮረ ተግባር ማከናወኑን ተናግረዋል፡፡

የከተማዋን ዕድገት የሚመጥን የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ስራም በቴክኖሎጂ አጋዥነት በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ በበኩላቸው ÷ የአዲስ አበባ ፖሊስ ያከናወናቸው የለውጥ ስራዎችን አድንቀዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.