ምክር ቤቱ የቀረበለትን ሞሽን አፀደቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክር ቤቱ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም በፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ የቀረበውን የ2017 የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫ ሞሽን አፀደቀ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብስባውን ዛሬ አካሂዷል፡፡
በፕሬዚዳንቱ የቀረበውን ሞሽን መነሻ በማድረግ ከምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን÷ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያና ምላሽ ተሠጥቶባቸዋል፡፡
በመጨረሻም ምክር ቤቱ የቀረበለትን ሞሽን አፅድቋል፡፡