Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ- ጂቡቲ የባቡር መስመር በሚያልፍባቸው የአፋር ክልል አካባቢዎችን አስመልክቶ ምክክር ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ጂቡቲ የምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር ስራ አስፈጻሚ ታከለ ዑማ (ኢ/ር) ከአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ጋር ኢትዮ- ጂቡቲ የባቡር መስመር በሚያልፍባቸው የክልሉ አካባቢዎች ላይ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ተወያይተዋል፡፡

ታከለ ዑማ(ኢ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መረጃ ከአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ጋር መወያየታቸውን አንስተዋል፡፡

በውይይቱም ፥ ኢትዮ- ጂቡቲ የባቡር መስመር በሚያልፍባቸው የክልሉ አካባቢዎች ላይ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉን ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል::

ታከለ ዑማ(ኢ/ር) የባቡር ደህንነት እና የተለያዩ አገልግሎቱን አደጋ ላይ የሚጥሉ ችግሮችን ለመፍታት ላሳዩት ቁርጠኝነትም ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባን አመስግነዋል፡፡

የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ለደንበኞቹ ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችለው በየአካባቢው ካሉ የማህበረሰብ ክፍሎች እና የመንግስት ኃላፊዎች ጋር እንደሚሰራም ነው የጠቆሙት፡፡

ባቡሩ በሚያልፍበት አካባቢዎች ያሉ መሰረተ ልማቶች እንዲጠበቁ እየተባበሩ ያሉ አካላትንም አመስግነዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.