ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ያላትን አጋርነት ታጠናክራለች – ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ያላትን አጋርነት እንደምታጠናክር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ዕውቅና ለተሰጣቸው የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች የአቀባበል ስነ ስርዓት አድርገዋል፡፡
በሥነ-ስርዓቱም ኢትዮጵያ ከሀገራት ጋር እና ድርጅቶች ጋር ያላትን አጋርነት እንደምታጠናክር መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡