Fana: At a Speed of Life!

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኖርዌይ ፓርላማ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኖርዌይ ፓርላማ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።

የሰልፉ ዋና ምክንያት እና ዓላማ በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ የተፈፀመውን ግድያ ተከትሎ በሽብርተኛ ተግባር ላይ በተሰማሩ አካላት ንፁሃን ኢትዮጵያውያን ሕይወት መቀጠፉ፣ ንብረት መውደሙና መፈናቀላቸውን በመቃወም ነው።

በሰልፉ ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያንም የድርጊቱ ፈፃሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ የጠየቁ ሲሆን፥ በሃጫሉ ላይ የተፈፀመውን ግድያም አውግዘዋል።

የሰልፉ አስተባባሪ አቶ ጌታቸው በቀለ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በሰልፉ ላይ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያን ኖርዌይ በኢትዮጵያ የተጀመረው ለውጥ እንድትደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይም የኢትዮጵያውያን ጥያቄ በተመለከተ ለኖርዌይ ፓርላማ የተዘጋጀ ደብዳቤ ከፓርላማ ለተወከሉት ተወካይ ተሰጥቷል።

በተጨማሪም ደብዳቤው ለኖርዌይ የውጭ ዱጋይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳይ ዴስክ እና በኖርዌይ ለኢትዮጵያ አምባሳደር መላኩንም የሰልፉ አስተባባሪ ተናግረዋል።

በሰልፉ ላይ ተገኝተው ደብዳቤውን የተቀበሉት በኖርዌይ የፓርላማ የክርስቲያን ዲሞክራት ፓርቲ ተወካይ ዮርን ኤልሳቤት፥ “የኢትዮጵያን ዲሞክራሲያዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሂደት ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ኃይሎች ጎሳን መሰረት ላደረገ እና በኃይል በታገዘ ሁከት ባስነሱት አመፅ ለጠፋው የሰው ሕይወት ተጠያቂ ናቸው” ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በጥፋት ሀይሎች ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ የሚደነቅ መሆኑንም ተናግረዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.