Fana: At a Speed of Life!

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በባሕር ዳር ከተማ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በባሕር ዳር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ፡፡

በጉብኙት ወቅት ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በተጨማሪ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም የዓባይ ድልድይን፣ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታን፣ የባሕር ዳር ከተማ የኮሪደር ልማት እና ሌሎች የልማት እንቅስቃሴዎችን ተመልክተዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በክልሉ ወቅታዊ የሰላም ሁኔታዎች እና የሕዝቡን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በሚከናወኑ ሥራዎች ላይ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር መምከራቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

የውይይቱ ዓላማም የክልሉ ሰላም በዘላቂነት እንዲረጋገጥ፣ ሕዝቡም የተረጋጋ ኑሮን እንዲመራ እና ሙሉ አቅሙን በልማት ሥራዎች ላይ እንዲያውል ለማድረግ መሆኑን ተጠቅሷል፡፡

በዚሁ ወቅትም የክልሉ ሕዝብ ከጸጥታ መዋቅሮች ጋር በመቀናጀት ሰላሙን የሚያደፈርሱ አካላትን መከላከል ሰላምን ማስፈን እንደሚጠበቅበት ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.