Fana: At a Speed of Life!

ፓርቲው የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በመገንባት ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ብልጽግና ፓርቲ የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በማደስና በመገንባት ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለፁ።

የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት በአሶሳ ከተማ ለአቅመ ደካሞች ያስገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች ያስረከበ ሲሆን÷ ቤቶቹም ሙሉ የቤት መገልገያ ቁሳቁስ የተሟላላቸው እንደሆኑ ተገልጿል።

አቶ አደም በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት÷ ብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮር ስራዎችን በልዩ ትኩረት እየሰራ ፤ በዚህም የአቅመ ደካማ ቤቶችን በመገንባት ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡

ሰው ተኮር ስራዎችና ቃልን በተግባር መፈፀም የፓርቲው መለያ መሆኑን ጠቅሰው÷ በየደረጃው ያሉ የብልጽግና ፓርቲ መዋቅሮች አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በተጠናከረ መልኩ መወጣት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ፓርቲው የዜጎችን ፍትሐዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ቤታቸው የታደሰላቸውና እንደ አዲስ የተገነባላቸው ነዋሪዎች ለተደረገላቸው የቤት እድሳትና ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.