Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ ለመከላከል እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው ከፌደራል መንግስት ጋር የግሪሳ ወፍ መንጋን ለመከላከል በትብብር እየተሰራ መሆኑን አስታውቆ ከግብርና ሚኒስቴርም የባለሙያዎች ልዑክ ወደ ክልሉ መላኩን ገልጿል፡፡

ልዑኩ የግሪሳ ወፍ መንጋ ወደሚገኝበት አካባቢ በመሄድና ህዝቡን በማስተባበር የግሪሳ ወፍ መንጋን ለመበተን እየሰራ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ከሚኒስቴሩ የተላኩ የኬሚካል መርጫ ተሽከርካሪዎች እና አስፈላጊ ግብዓቶች እንደተላኩ የተገለጸ ሲሆን÷ ዛሬ አመሻሽ ላይ የኬሚካል ርጭት ስራ እንደሚከናወን ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም በአውሮፕላን ዛሬ ማታ የግሪሳ ወፍ መካለከያ ኬሚካል ለመርጨት የወፍ መንጋው የሚያድርበት አካባቢ ተለይቷልም ነው የተባለው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.