ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት ካላት ቁርጠኝነት አንጻር ብልጽግናን ማረጋገጥ የሁሉም ዜጎች የወል እውነት ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት ካላት ቁርጠኝነት አንጻር ብልጽግናን ማረጋገጥ የሁሉም ዜጎች የወል እውነት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ብልጽግና ፓርቲ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እንዲሁም እውነት፣ እውቀትና ጥበብን መለያው አድርጎ ባለፉት አምስት ዓመታት ፈተናዎችን ወደ ድል በመቀየር በርካታ ስኬቶችን አስመዝግቧል ብለዋል።
በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች የተመዘገቡ ድሎችም የዜጎችን ተጠቃሚነት በተግባር ያረጋገጡ መሆናቸውንም አንስተዋል፡፡
በቀጣይ አምስት ዓመታት ደግሞ አዳዲስ ድሎችን በማስመዝገብ ከራሷ አልፋ ለሌሎች የምትተርፍ ሀገር ለመገንባት እንሰራለን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡