Fana: At a Speed of Life!

በለንደን ደርቢ አርሰናል ዌስትሃም ዩናይትድን 5 ለ 2 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ አምስት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡

ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ ወደ ለንደን ስታዲየም በማቅናት ዌስትሃም ዩናይትድን የገጠመው አርሰናል 5 ለ 2 በሆነ ሰፊ ልዩነት አሸንፏል፡፡

የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ጋብሬል ማጋሌሽ፣ ትሮሳርድ፣ ኦዴጋርድ ፣ ሃቨርትዝ እና ሳካ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

የዌስትሃም ዩናይትድን ግቦች ደግሞ ኤመርሰን እና አሮን ዋን ቢሳካ አስቆጥረዋል፡፡

በተመሳሳይ 12 ሰዓት በተደረጉ ጨዋታዎች ብሬንትፎርድ ሌስተር ሲቲን 4 ለ1፣ ቦርንሞውዝ ዎልቭስን 4 ለ 2 እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ኢፕስዊች ታውንን 1 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡

በሌላ በኩል ክሪስታል ፓላስ እና ኒውካስል ዩናይትድ ያደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎአርሰናል በ25 ነጥብ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ሁለተኛ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.