Fana: At a Speed of Life!

ዚምባብዌ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የወጣውን ደንብ የተላለፉ ከ105 ሺህ በላይ ሰዎችን አሰረች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዚምባብዌ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የወጣውን ደንብ የተላለፉ ከ105 ሺህ በላይ ሰዎችን አሰረች፡፡

የሃገሪቱ መንግስት ከውጭ ሃገራት ወደ ዚምባብዌ የሚገቡ ዜጎች በተዘጋጁ የማቆያ ስፍራዎች ለሶስት ሳምንታት እንዲቆዩ ያስገድዳል፡፡

ይሁን እንጅ 276 ሰዎች ከእነዚህ ለይቶ ማቆያ ስፍራዎች ማምለጣቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም 30 የሚሆኑት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ቫይረሱን ወደ ማህበረሰቡ በማስተላለፍ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ይታያልም ነው ያለው፡፡

ከሰሞኑም ፖሊስ የተጣሉ ክልከላዎችን ተላልፈዋል ያላቸውን ሰዎች በቁጥጥር ስር እያዋለ ሲሆን ባለፉት ሁለተ ቀናት ውስጥም ከ1 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎችን አላስፈላጊ እንቅስቃሴ በማድረግ ወይም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ባለማድረግ ማሰሩን ገልጿል፡፡

ተፎካካሪ ፓርቲዎች ደግሞ የመንግስት እርምጃ እነርሱን ለማዳከም በምክንያት የተደረገ ነው ሲሉ ይወነጅላሉ፡፡

በሃገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚል መንግስት ጥሎት የነበረው ክልከላ አሁን ላይ እየላላ መምጣቱ ይነገራል፡፡

በዚምባብዌ ከ1 ሺህ 500 በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ምንጭ፣ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.