Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል መንግስትና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ስምምነት ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው – ሰላም ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል መንግስትና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል የተካሄደው ስምምነት ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ መንገድ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የሰላም ስምምነት መፈራረሙ ለሀገራችን ዘላቂና አዎንታዊ ሰላም መረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብሏል።

በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ መካከል የተካሄደው የሰላም ስምምነት እጅግ የሚደነቅ መሆኑን ገልጿል።

ሂደቱ የሰላም መንገድ ሌላ አማራጭ የሌለው ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ መንገድ መሆኑንም የሚያመለክት ነው በማለት ገልጿል።

የኦሮሞ ህዝብ በተደጋጋሚ ላደረገው የሰላም ጥሪ ተገቢ ምላሽ በመስጠትና በመቀበል የተደረገው የሰላም ስምምነት ለዘላቂና አዎንታዊ ሰላም መረጋገጥ አበርክቶ ያለው በመሆኑ ሚኒስቴር በአድናቆት የሚመለከተው መሆኑን አመልክቷል።

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ልዩነቶችን በዘመናዊ መንገድ በውይይትና በሰላም ለመፍታት የሚደረጉ መሰል ጥረቶች ሁሉ እንዲሳኩ ሚኒስቴሩ የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት አረጋግጧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.