Fana: At a Speed of Life!

 አየር መንገዱ ለአፍሪካ አቪዬሽን ልህቀት እያበረከተ ላለው አስተዋፅዖ ሽልማት ተበረከተለት

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ በርካታ መዳረሻዎች የበረራ አገልግሎት በመስጠት የአፍሪካን አቪዬሽን ኢንዱስትሪ በማሳደግ ረገድ ላለው ቁርጠኝነት እና ለአቪዬሽን ልህቀት እያበረከተ ላለው አስተዋፅዖ የዕውቅና ሽልማት ተበረከተለት።

አየር መንገዲ ሽልማቱ የተበረከተለት ከአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽን (ኤኤፍሲኤሲ) ነው።

በኮንጎ ሪፐብሊክ ብራዛቪል ከተማ በተካሄደው 35ኛው የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽን ጉባኤ ላይ ሽልማቱ የተበረከተለት ሲሆን፤ በመድረኩ የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ ኤርፖርትም በፈረንጆቹ ከ2022 እስከ 2024 ዓ.ም ባስተናገደው ከፍተኛ የመንገደኞች ቁጥር ዕውቅና ተሰጥቶታል።

ኤኤፍሲኤሲ በአፍሪካ ሕብረት ስር የሚተዳደርና የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ጉዳዮችን የሚከታተል ልዩ ኤጀንሲ ሲሆን በሶስት አመት አንድ ግዜ ጠቅላላ ጉባኤውን እንደሚያደርግ የአየር መንገዱ መረጃ ጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.