Fana: At a Speed of Life!

አንድነታችንን ለመናድ ያሰቡ ባንዳዎች ህልም በመከላከያ ሠራዊትና በህዝባችን ትብብር ከሽፏል – ሌ/ጄ ሹማ አብደታ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ጠላቶች ተደግፈው አንድነታችንን ለመናድ ያሰቡ ተላላኪ ባንዳዎች ህልም በመከላከያ ሠራዊትና በህዝባችን ትብብር ከሽፏል ሲሉ የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ገለጹ፡፡

ሌ/ጄ ሹማ አብደታ የካራማራ ኮርስ ሰልጣኝ ኮማንዶዎች ጋር በተወያዩበት ወቅት እንዳሉት÷ ህዝብን የጥቃታቸው ማዕከል አድርገው የሚንቀሳቀሱ አሸባሪና ፅንፈኛ ሀይሎች አከርካሪያቸው ተመትቶ የተሻለ የሠላም ሁኔታ እየተፈጠረ ይገኛል።

የእነዚህ ኃይሎች ድርጊት ሀገርን ለትርምስና ለብጥብጥ፤ ዜጎችን ለስደትና ለእልቂት እንደሚያጋልጥ ጠቅሰው፤ በህዝብ ጥያቄ ስም የሚያራምዱት ጎጠኝነት፣ አክራሪ ብሔረተኝነት እና ነጠላ ትርክት ለህዝቦች አንድነትና ለሀገር ህልውና አደገኛ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

እነዚህ አስተሳሰቦች በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጭምር እየተደገፈ በተላላኪ ባንዳዎች ታጥቆ የሀገራችንንና የህዝቦቻችንን አንድነት ለመናድ ቢታሠብም በሀገር ወዳዱ የመከላከያ ሠራዊትና በህዝባችን ህልማቸው እየከሸፈ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የኮማንዶና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል ሀገር አሻጋሪ ጀግና አመራሮችና ተዋጊ የኮማንዶ፣ የአየር ወለድና የፀረ-ሽብር ልዩ ሀይል አናብስቶች መፍለቂያ መሆኑንም መግለጻቸውን የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡

የካራማራ ኮርስ ኮማንዶ ሠልጣኞች የኢትዮጵያንና የሕዝቦቿን ዕድገትና ብልፅግና ለማደናቀፍ የሚሞክረውን ማንኛውንም ሀይል በመመከት የአባቶቻቸውን ታሪክ ማስቀጠል እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.