Fana: At a Speed of Life!

ፓርቲዎች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለአንድ ዓመት ሲያደርጉት የነበረው ውይይት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስተባባሪነት በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በተመረጡ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሲደረግ የነበረው ውይይት መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያም አምስቱ የምርጫ ቦርዱ አመራር አባላት፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረ ሥላሴ፣ የውይይቱ ተሣታፊ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ታዛቢዎች ተገኝተዋል፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በዚሁ ወቅት÷ ሲደረግ የነበረው ውይይት ለሀገር ግንባታ ሂደትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መጎልበት ተስፋ የሚሰጥ ነው ማለታቸውን የምርጫ ቦርድ መረጃ አመላክቷል፡፡

ተሳታፊ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ከቆሙለት ዓላማ ባሻገር የሌሎችን ሐሳብ ለመስማትና ለማስተናገድ ዝግጁ ሆነው የቀረቡበት እንዲሁም የራሳቸውን ሐሳብ በነፃነት ያጋሩበት መድረክ እንደነበርም አውስተዋል፡፡

የውይይቱ ዓላማ ፓርቲዎች የሚወያዩበትን መድረክ መፍጠርና በሂደቱም የዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ማጎልበት እንደነበር ያስገነዘቡት ደግሞ የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ ናቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.