አቶ ጥላሁን ከበደ በአርባ ምንጭ ሀገር አቀፍ የንግድ ትርዒትና ባዛርን ከፈቱ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በአርባ ምንጭ ከተማ የተዘጋጀውን ሀገር አቀፍ የንግድ ትርዒትና ባዛር በይፋ ከፍተዋል፡፡
ለአንድ ሳምንት የሚቆየው የንግድ ትርዒትና ባዛሩ 19ኛውን የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን አስመልክቶ እንደተዘጋጀ ተገልጿል፡፡
በንግድ ትርዒትና ባዛሩ ላይ ኢንተር ፕራይዞችና ከመላው የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ ከ150 በላይ የንግድ ተቋማት እንደተሳተፉም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የንግድ ትርዒትና ባዛሩ ከንግድና ማህበራት ዘርፍ ምክር ቤት ጋር በመቀናጀት መዘጋጀቱም ተመላክቷል።