ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ የቻይና ሕዝባዊ የፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የቻይና ሕዝባዊ የፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ፓን ቺፒንግን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከምክትል ፕሬዚዳንት ፓን ቺፒንግ ጋር ባደረጉት ውይይት÷ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትምህርትና ስልጠና በተለይ በፎረንሲክ ምርመራ፣ በድሮን ኦፕሬሽን፣ በስማርት ፖሊሲንግ በሁነት አስተዳደር እንዲሁም በቪ.አይ.ፒ ጥበቃ ዙሪያ በቅንጅት ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
መጪው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤን ደኅንነት በተገቢው ሁኔታ ለማስጠበቅ በቪ.አይ.ፒ ጥበቃ እና በዓለም አቀፍ ሁነት አስተዳደር ዙሪያ ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አመሮችና አባላት ስልጠና የሚሰጡ ባለሙያዎችን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚልኩ ፓን ቺፒንግን ቃል ገብተዋል፡፡