Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ብናልፍ  አንዱአለም አዲስ ለተሾሙት የሰላም ሚኒስትር የሥራ ርክክብ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር አምባሳደር ብናልፍ  አንዱአለም አዲስ ለተሾሙት የሰላም ሚኒስትር አቶ መሐመድ እድሪስ የሥራ ርክክብ አድርገዋል፡፡

 

አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ለተደረገላቸው አሸኛኘት አመሰግነው  አመራርነት የተለየ ዋጋ የሚያስከፍል እና የተለየ እድል ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

አምባሳደር ብናልፍ  ልምዳቸውንም ያካፈሉ ሲሆን÷ በተቋሙ በነበራቸው ጊዜ ብዙ ስኬት የተመዘገቡበት እና ብዙ ፈተናዎች ያለፉበት ጊዜ  እንደነበር አንስተዋል።

 

የሰላም ሚኒስትር አቶ መሐመድ እድሪስ በበኩላቸው÷ ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው ስለ ሰላም ለመስራት ዕድል በማግኝቴ ዕድለኛ ነኝ ብለዋል።

 

በቆይታዬ ትልልቅ ሥራዎችን የምናከናውንበት  እንደሚሆን አምናለሁ ያሉት  አቶ መሐመድ  ለአምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም መልካም የስራ ዘመን መመኘታቸውን የሰላም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.