Fana: At a Speed of Life!

የመጀመሪያው የፓርላማ የዜጎች ፎረም ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ሀገራዊ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የመጀመሪያው የፓርላማ የዜጎች ፎረም ተካሂዷል፡፡

በፎረሙ ላይም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የምክር ቤት አባላት፣ ሚኒስትሮች፣ ምሁራን፣ የሚዲያ ተቋማት ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

አፈጉባዔ ታገሰ ጫፎ÷ ፎረሙ ለቀጣይ ሀገራዊ ብልጽግና የሚያግዙ ትልልቅ ሃሳቦች የሚፈልቁበት መድረክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መድረኩ ትብብር እና መከባበር እንዲጎለብት የሚያስችሉ እድሎችን መፍጠር ያለመ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በመድረኩ የተመረጠው ዋነኛ ርዕስ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሆኑን ጠቁመው÷ ግድቡ በአፍሪካ ትልቁ የሃይል ማመንጫ ከመሆኑ ባሻገር የመቻላችንና የተስፋ ብርሃናችን ምልክት ነው ብለዋል።

የፓርላማ ዜጎች ፎረም በቀጣይ በየወሩ ለሀገርና ለአህጉሪቷ በሚበጁ ቁልፍ አጀንዳዎች ዙሪያ እንደሚካሄድ ተመላክቷል፡፡

በበረከት ተካልኝ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.