Fana: At a Speed of Life!

የብሔራዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት በዛሬው ዕለት አራተኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡

ምክር ቤቱ በሶስተኛ መደበኛ ስብሰባው እንዲፈፀሙ ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች መሠረት የተሠሩ ሥራዎችንና አስፈላጊ የሆኑ የኮሚቴ አደረጃጀቶች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገልጸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፥ ከውሳኔው በተጨማሪ ለዲጂታል ኢትዮጵያ አስፈላጊ የሆኑ የብሔራዊ ኤሌክትሮኒክ መንግስት ስትራቴጂና የብሔራዊ ኤሌክትሮኒክ ንግድ ስትራቴጂ ሰነዶች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል ብለዋል፡፡

የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ በእመርታ የሚያድግበት ዘመን ላይ እንደመሆኑ፤ ምክር ቤቱም ለዚሁ ዕድገት ተገቢውን ሚና ለመወጣት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አንስተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.