ኢትዮጵያ ቡና አርባ ምንጭ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ10ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና አርባ ምንጭ ከተማን 2 ለ 0 አሸነፈ፡፡
10 ሠዓት ላይ በተከናወነው ጨዋታ ለኢትዮጵያ ቡና የማሸነፊያ ግቦቹን ከዕረፍት መልስ ዲቫይን ዋቹኩዋ እና ኦካይ ጁል አስቆጥረዋል፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 1 ሠዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ለባሕር ዳር ከተማ ግቦቹን ፍሬው ሰለሞን፣ ጄሮም ፊሊፕ እና ሙጂብ ቃሲም አስቆጥረዋል፡፡